በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • አገልግሎቶች
    • መርሐ ግብር
    • የህፃናት ጥምቀት
    • የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት
    • ፍትሐት
    • ክራዮች
  • የሰንበት ት/ቤት
  • ያግኙን
  • Norwegian
  • Menu Menu

እንኳን ለዳግም ትንሳዔ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ከተነሳ በኋላ የትንሳዔ ዕለት ለአስራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ለመጀመሪያ ጊዜ በመካከላቸው ተገኝቶ «ሰላም ለሁላችሁ ይሁን» ብሎ ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡ በኋላ ቶማስ ከሔደበት አገልግሎት ሲመለስ የጌታችንን መነሣትና እንደተገለጸላቸው ሐዋርያት በደስታ ሲነግሩት «በኋላ እናንተ ዐየን ብላችሁ ልትመሰክሩ፣ ልታስተምሩ፣ እኔ ግን «ሰምቼአለሁ» ብዬ ልመሰክር፣ ላስተምር? አይሆንም እኔም ካላየሁ አላምንም» በማለቱ ጌታችን መድኀኔዓለም ክርስቶስ ልክ እንደመጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በአንድነት በተዘጋ ቤት እንዳሉ ለሁለትኛ ጊዜ ተግልጾላቸዋል። በዚሁም መሰረት ለሁለተኛ ጊዜ ቶማስ ባለበት በግልጥ የታየበት ዕለት ሰለሆነ ቤተ ክርስቲያናችን ዳግም ትንሣኤ በማለት ይህንን ዕለት ታከብረዋለች፡፡

“ከስምንት ቀን በኋላም ደቀ መዛሙርቱ ደግመው በውስጥ ነበሩ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ። ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ። ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው”። ከዚያም በኋላ ቶማስን ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው። ቶማስም። ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት። ኢየሱስም። ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው። (የዮሐንስ ወንጌል – ምዕራፍ 20፥26-29)።

ስለዚህ ይህ ሰንበት የትንሣኤው ምስጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት ስለሆነ «ዳግም ትንሣኤ» ተብሎ ከትንሳዔ ባልተናነሰ መልኩ ይከበራል፡፡

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://lidetalemariam.no/a/wp-content/uploads/dagem_tensae1.jpg 480 480 webadmin@lidetalemariam.no https://lidetalemariam.no/a/wp-content/uploads/lm-logo.svg webadmin@lidetalemariam.no2024-05-11 12:58:132024-05-11 13:04:32እንኳን ለዳግም ትንሳዔ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በፌስቡክ ያግኙን

Search Search

Recent Posts

  • እንኳን ለዐብይ ጾም ዘወረደ በሰላም አደረሳችሁ
  • የሀዘን መግለጫና የጸሎት መርሐ-ግብር ጥሪ
  • ፆመ ፅጌ – ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭
  • ደመራ እና ብርሃነ መስቀሉ
  • ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል

Archives

  • June 2026
  • February 2026
  • October 2025
  • September 2025
  • July 2025
  • April 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
© የኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የዕመቤታችን ቅድስትድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በድምቀት ተከብሮ ዋለ Link to: የዕመቤታችን ቅድስትድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በድምቀት ተከብሮ ዋለ የዕመቤታችን ቅድስትድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ... Link to: በደብራችን ማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም የተዘጋጀ ታላቅ ኦርቶድክሳዊ ተዋህዶ የወጣቶች ጉባኤ! Link to: በደብራችን ማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም የተዘጋጀ ታላቅ ኦርቶድክሳዊ ተዋህዶ የወጣቶች ጉባኤ! በደብራችን ማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top