በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • አገልግሎቶች
    • መርሐ ግብር
    • የህፃናት ጥምቀት
    • የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት
    • ፍትሐት
    • ክራዮች
  • የሰንበት ት/ቤት
  • ያግኙን
  • Norwegian
  • Menu Menu

የሀዘን መግለጫና የጸሎት መርሐ-ግብር ጥሪ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
​“መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫውን ጨርሻለሁ፤ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ።” (2ኛ ጢሞ. 4፥7)
​እጅግ የምንወደውና የምናከብረው ወንድማችን ኢንጂነር መስፍን ኃይሌ፣ በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዚህች ዕለት
ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል። ወንድማችን ኢንጂነር መስፍን ኃይሌ ባለ ትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ አባት
የነበረ ሲሆን፤ በማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን
ምሥረታ ጀምሮ ቤተክርስቲያንን በፍጹም ቅንነት፣ በትጋትና በታማኝነት ሲያገለግል የቆየ
ተወዳጅ ወንድማችን ነበር። ቤተክርስቲያናችን በወንድማችን ማረፍ የተሰማትን ጥልቅና መራራ ሀዘን
እየገለጸች፤ ለባለቤቱ፣ ለልጁ እንዲሁም ለመላው ቤተሰቦቹና ወዳጅ ዘመዶቹ እግዚአብሔር አምላክ
መጽናናትን እንዲሰጥ ትጸልያለች።
​በመሆኑም የወንድማችንን ሕይወት የምናስብበትና ለቤተሰቦቹ የሀዘን ማጽናኛ የምንሰጥበት
መርሐ-ግብር በቤተክርስቲያናችን ደጀ-ሰላም ተዘጋጅቷል።
ወዳጅ ዘመዶቻችሁ ሁሉ በቦታው በመገኘት በጸሎትና በሐዘን እንድታጽናኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የማጽናኛ መርሐ-ግብር ሰዓታት፦
ቀን – የሰዓት ገደብ
ሐሙስ 05 Feb – ከ 18:00 – 21:00
ዓርብ 06 Feb – ከ 14:00 – 21:00
ቅዳሜ 07 Feb – ከ 14:00 – 21:00
እሁድ 08 Feb – ከ 14:00 – 21:00

አድራሻ – Caspar Storms vei 12, Oslo

የወንድማችንን ነፍስ በአብርሃም በይስሐቅና በያዕቆብ እቅፍ ያኑርልን።
​ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://lidetalemariam.no/a/wp-content/uploads/የሀዘን-መግለጫ_ኢንጂነር.jpg 3508 2481 webadmin@lidetalemariam.no https://lidetalemariam.no/a/wp-content/uploads/lm-logo.svg webadmin@lidetalemariam.no2026-02-06 11:58:172026-02-06 15:42:32የሀዘን መግለጫና የጸሎት መርሐ-ግብር ጥሪ

በፌስቡክ ያግኙን

Search Search

Recent Posts

  • የሀዘን መግለጫና የጸሎት መርሐ-ግብር ጥሪ
  • ፆመ ፅጌ – ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭
  • ደመራ እና ብርሃነ መስቀሉ
  • ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል
  • ጸሎት

Archives

  • February 2026
  • October 2025
  • September 2025
  • July 2025
  • April 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
© የኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ፆመ ፅጌ – ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭ Link to: ፆመ ፅጌ – ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭ ፆመ ፅጌ – ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭
Scroll to top Scroll to top Scroll to top