ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች
በአባልነት ለመመዝገብ የምትፈልጉ የአባልነት ፎርምና ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት
የባንክ ሂሳብ ቁጥር፡ 1503 622 909
111030
በቋሚነት
በቋሚነት በየወሩ በቀጥታ በባንክ አካውንት ወይንም በቪፕስ ለመክፈል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ የማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ በጥቂት ግለሰቦች አነሳሽነትና በእግዚአብሔር ፈቃድ መጋቢት 6 ቀን 2007 ዓ/ም ተመሠረተ፡፡ በወቅቱ የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ እንጦስ በቦታው ተገኝተው ቤተ ክርስቲያኑን ባርከውና ቀድሰው መሠረት ከመጣላቸውም በላይ በቀጣይነት ከአንድ ዓመት በኋላ የሊቀ መላኩን የቅዱስ ገብርኤል ጽላት በማስመጣት ለቤ/ክርስቲያኑ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ሲመሰረት 19 ምዕመናንና ምዕመናት በአባልነት ተመዝግበው የነበሩት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የአባላት ቁጥር ከ200 በላይ ሆኗል፡፡ ቋሚ ቤ/ክ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ለጊዜው በኪራይ ቀደም ሲል በካምፐን ሜኒሄትስ ሁስና በካምፐን ሺርከ አሁን ደግሞ በCaspar Storms vei 12, 0664 Oslo, የሰንበት ቅዳሴ፣ የሰንበት ት/ቤትና እንዲሁም የበዓላት መርሃ ግብር ሳይታጎሉ ቤተ ክርስቲያኑ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ ያልተቋረጠ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
ፎቶ፦ ብጹዕ አቡነ እንጦስ ቤተክርስቲያናችህንን ባርከው አገልግሎት ሲያስጀምሩ
የዘንድሮ 2017 ዓ/ም የጥምቀት በዓል ቅዳሜ ጥር 10 እና ዕሑድ ጥር 11 ቀን 2017 ዓ/ም (18. og 19. januar 2025) በበርገን መንበረ ልዑል ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ትክብሮ ይውላል!
የዘንድሮ 2017 ዓ/ም የጥምቀት በዓል እንደወትሮው በኖርዌይ ውስጥ በሚገኙ ትላልቅ አድባራት ማለትም
– የበርገን መንበረ ልዑል ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ
– የስታቫንገር ደብረ ገነት መድሃኔ አለም ወኪዳነ ምህረት ቤ/ክ
– የኦስሎ ማህደረስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ
– የክርስቲያንሳንድ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ
-የትሮንድሐይም ምስራቀ ጸሃይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ታቦታት በጋራ በተሳተፉበት በበርገን መንበረ ልዑል ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ አዘጋጅነት በበርገን ከተማ (Vilhelm Bjerknes vei 24, 5081 Bergen) ቅዳሜና ዕሑድ ጥር 10 እና 11 ቀን 2017 ዓ/ም (18. og 19. januar 2025) በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ይውላል።
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ቤዛ ኩሉ አለም ዮም ተወልደ / የዓለም ሁሉ ቤዛ ዛሬ ተወለደ!
የዘንድሮን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ ሰኞ ታህሳስ 28 ቀን 2024 ዓ/ም ከምሽቱ 20:00 ሰዓት ጀምሮ በማህሌት፣ በዝማሬ፣ በቅዳሴና ሌሎች የተለያዩ መርሃ ግብሮች በቤተ ክርስቲያናችን ተከብሮ ይውላል።
በኦስሎና አካባቢው የምትገኙ ምዕመናንና ምዕመናት በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ተገኝታችሁ በዓሉን በጋራ እንድናከብር የደብሩ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ በማክበር ይጋብዛል!
እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።” መዝ. 33፡7
የዘንድሮው የታህሳስ ወር የሊቀ መላዕክት የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በቤተ ክርስቲያናችን ቅዳሜ ታህሳስ 19 ቀን (28. desember 2024) ከዋዜማው ከሌሊቱ 01፡00 ሰዓት ጀምሮ በማህሌት፣ በዝማሬ፣ በስብከተ ወንጌል፣ በቅዳሴና በታቦተ ንግስ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ይውላል። በዕለቱም የቤተ ክርስቲያኒቱ የ5 ዓመት (2025 – 2030) መሪ ዕቀድ ለምዕመናንና ምዕመናት ቀርቦ ይጸድቃል።
በኦስሎና አካባቢው የምትገኙ ምዕመናንና ምዕመናት በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ተገኝታችሁ በዓሉን በድምቀት በማክበር የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የደብሩ የሰባካ መንፈሳዊ አስተዳደር በማክበር ይጋብዛል።
ጾመ_ነቢያት!
እግዚአብሔር አምላካችን ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ መልበሱን፣ ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ወደ ግብጽ ግብር መሰደዱን፣ በባሕረ ዮርዳኖስ መጠመቁን፣ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ማብራቱን፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል ልዩ ልዩ ዓይነት መከራ መቀበሉን፣ መሰቀሉን፣ መሞቱን፣ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ ማረጉንና ዳግም ለፍርድ የሚመጣ መኾኑን በአጠቃላይ የማዳን ሥራውን በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው አስቀደመው በትንቢት ተናግረዋል፡፡
የአምስት ዓመት መሪ እቅድ (2025 – 2030)
የማሀደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ ከ 2025 – 2030 የአምስት ዓመት መሪ ዕቅድ የተዘጋጀውን ረቂቅ ማብራሪያ በመስጠት ከቤተ ክርስቲያኒቱ ምዕመናን እና ምዕመናት ጋር በዛሬ ዕለት ዕሑድ ጥቅምት 10 ቀን ከሰንበት ቀዳሴ ሥነ ስርዓት በኋላ ዉይይት ተደርጓል፡፡ በዚሁም መሰረት የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው መልስ የተሰጠባቸው ሲሆን ለመሪ ዕቅዱ እንደግብአት የሚጠቅሙ ሃሳቦችም ተሰንዝረዋል።
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!
“የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።” 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡18
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤ/ክ በየዓመቱ መስከረም 16 ቀን (26. september) የመስቀል በዓል በዋዜማው የደመራን ችቦ በማብራት በደመቀ ሁኔታ ይከበራል፡፡ በዓሉ የንጉስ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ፣ ደመራ አስደምራ በእሳት ባቀጣጠለችው ጊዜ፣ ጢሱ ወደ ላይ ከወጣ በኋላ ተመልሶ ያረፈበትን ሥፍራ አስቆፍራ ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ማግኘቷን በማስመልከት በየዓመቱ የሚከበር ታላቅ ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓል ነው፡፡
እንኳን ከዘመነ ዮሃንስ ወደ ዘመነ ማቴዮስ በሰላም እና በጤና አሸጋገራችሁ!
“በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል” መዝ – ምዕራፍ 65:11
አዲሱ ዘመን የሰላም የጤና የንስሀ እንዲሆንላችሁ እየተመኘን አዲሱን ዘመን በማስመልከት በዕለቱ ረቡዕ መስከረም 1 ቀን ከቀኑ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በቅዳሴ እና በዝማሬ እንዲሁም በትምህርተ ወንጌል በደብራችን በማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ይከበራል።
በኦስሎና አካባቢዋ የምትገኙ ምዕመናንና መዕመናት በቦታው በመገኘት የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የደብሩ ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጽህፈት ቤት በማክበር ይጋብዛል።
የስዊድን፤ ስካንዲናቪያን እና ግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት የ2016 ዓ/ም ጠቅላላ ጉባኤ
በስዊድን፤ ስካንዲናቪያን እና ግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ጷጉሜ 1 እና 2 ቀን 2016 ዓ/ም በስቶክሆልም መንበረ ጵጵስና ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ሲያካሄድ የቆየውን ጠቅላላ ጉባኤ አጠንቆ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
ጷጉሜ(ጷጉሜን) እንኳን ለትንሿ የበረከት ውርሃ ጳግሜ በሰላም አደረሳችሁ!
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጷጉሜን የወር ተጨማሪ ሳይሆን የዓመት ተጨማሪ በማድረግ ወሮቹን 30 ቀን፣ የዓመቱንም ቀን ቁጥር ደግሞ ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ቀን አድርገው ሰይመውታል፡፡ ጷጉሜን የሚለው ስያሜዋ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን “ኤፓጉሜኔ” ማለት ጭማሪ ማለት ነው ፡፡ በግእዝ ቋንቋችን ተውሳክ ማለት ነው፡፡ ተውሳክ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው፡፡
በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጷጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡
እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
የደብረ ታቦር (የቡሄ) በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤ/ክ ቀኖና መሰረት ከዘጠኙ አብይ በዓላት ውስጥ አንዱ ሲሆን የሚከበረውም ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በማስተማር በነበረበት ጊዜ በደብረ ታቦር ላይ ብርሃነ መለኮቱን ክብረ መንግስቱን የገለፀበት ዕለትን ለማስታወስ ነው። ይህ በዐል በየአመቱ ነሃሴ ፲፫ (13) ቀን ይከበራል።