እንኳን ለዐብይ ጾም ዘወረደ በሰላም አደረሳችሁ

እንኳን ለዐብይ ጾም ዘወረደ በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን፡፡

ዐቢይ ጾም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ ከተጠመቀ በኋላ ዐርባ ቀን የጾመው፤ እኛም እንድንጾማቸው በቤተ ክርስቲያናችን ከታዘዝናቸው ሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ ነው፡፡ ምእመናን ጌታችን ያደረገውን ምሳሌ ተከትለን ጾሙን በየዓመቱ እንጾመዋለን፡፡