የዘንድሮ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በድምቀት ተከበረ!

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!
ቤዛ ኩሉ አለም ዮም ተወልደ / የዓለም ሁሉ ቤዛ ዛሬ ተወለደ!
የሃይማኖት አባቶቻችን «እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጥበብ ይልቅ በጥፋቱ ወድቆ የነበረውን ዓለም ያዳነበት ጥበቡ ይደንቃል» ይላሉ፡፡
- እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። የሉቃስ ወንጌል – ምዕራፍ 2:10-11
 - የፍጥረቱቲ መሪ የትሩፋት ጀማሪ ይሆን ዘንድ ሰው ሆነ፡፡ ዮሐ. 13፣14፡፡
 - ሕዝብና አሕዛብን አንድ ሊያደርግ እግዚአብሔር ሰው ሆነ፡፡ ገላ. 3፡28፡፡
 - ሞትን በሞቱ ይሽረው ዘንድ እግዚአብሔር ሰው ሆነ፡፡ 1ቆሮ. 1፡20፡፡
 - በሥጋ ከይሲ ተሰውሮ የመጣውን ዲያብሎስን በመስቀሉ ድል ይነሳው ሥልጣኑንም ይገፍፈው ዘንድ ሰው ሆነ፡፡ ቆላ. 2፡14፡፡
 - ሀብታም ሲሆን፣ እኛ በእርሱ ድህነት ባለጠጎች እንሆን ዘንድ ስለእኛ ድሀ ሆነ፡፡ 2ቆሮ. 8፡9፡፡
 - አዳምን ወደ ክብር ቦታው ለመመለስ እርሱ ማደሪያ ስፍራ አጥቶ በግርግም /በከብቶች በረት – በበጎች ጉረኖ/ ተወለደ፡፡ ሉቃስ 2፡7፡፡
 
የዘንድሮን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ከዋዜማው ከቅዳሜ ታህሳስ 27 ቀን 2016 ዓ/ም (06. januar 2024) ከምሽቱ 19:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ዕሑድ ጠዋት ድረስ በማህሌት፣ በዝማሬ፣ በስብከት፣ በቅዳሴና ሌሎች በተለያዩ መርሃ ግብሮች በታላቅ ድምቀት ተክብሮ ዋለ፡፡