በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • አገልግሎቶች
    • መርሐ ግብር
    • የህፃናት ጥምቀት
    • የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት
    • ፍትሐት
    • ክራዮች
  • የሰንበት ት/ቤት
  • ያግኙን
  • Norwegian
  • Menu Menu

የጌታችን የመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በስታቫንገር ከተማ በድምቀት ተከብሮ ዋለ!

የጥምቀት በዓል ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ በማየ ዮርዳኖስ መጠመቁን ለመዘከር የሚከበር በዓል ነዉ፡፡ ጥምቀት ከእግዚአብሔር ዳግም የምንወለድበት፣የቤተ ክርስቲያን አባል የምንሆንበት፣ የኃጢያት ስርየትና የስጋ ፈውስ የምናገኝበት፣  ነጻነታችን የታወጀበት፣ የዕዳ ደብዳቤአችን የተቀደደበት፣ የባርነት ቀንበር የተሰበረበት፣ ምስጢረ ሥላሴ የተገለጠበት ረቂቅ ምስጢር ነው።

ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀትን የመሠረተው በሦስት መንገድ ነው።

  • መጀመሪያ በተግባር ራሱ ተጠምቆ እንድንጠመቅ አስተምሮናል፤ አርአያም ሆኖናል (ማቴ 3፡13)፡፡
  • ሁለተኛም በትምህርቱ “ያመነ የተጠመቀ ይድናል” (ማር 16፡16) እንዲሁም “እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔር መንግሥት ሊያይ አይችልም” (ዮሐ 3፡3-6) በማለት ጥምቀት ለድኅነት አስፈላጊ መሆኑን አስተምሯል፡፡
  • ሦስተኛም ለቅዱሳን ሐዋርያት በሰጣቸው ትዕዛዝ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” (ማቴ 28፡19-20) በማለት  ምስጢረ ጥምቀትን መስርቶልናል። ይህንንም መሠረት በማድረግ ሃይማኖታቸው የቀና ቅዱሳን አባቶች “ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኀጢአት፣ ኀጢአትን በምታስተሠርይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን” በማለት መሠረተ እምነትን ደንግገዋል፡፡

የዘንድሮ የጥምቀት በዓል እንደወትሮው በኖርዌይ ውስጥ በሚገኙ ትላልቅ አድባራት ማለትም

  • የስታቫንገር ደብረ ገነት መድሃኔ አለም ወኪዳነ ምህረት ቤ/ክ
  • የኦስሎ ማህደረስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ
  • የክርስቲያንሳንድ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ
  • የበርገን መንበረ ልዑል ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ
  • የትሮንድሐይም ምስራቀ ጸሃይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ታቦታት በጋራ በተሳተፉበት በስታቫንገር ደብረ ገነት መድሃኔ አለም ወኪዳነ ምህረት ቤ/ክ አዘጋጅነት በስታቫንገር ከተማ (Sunde og Kvernevik bydelshus, Traneveien 10, Hafrsfjord) ቅዳሜና ዕሑድ ጥር 11ና 12 ቀን 2016 ዓ/ም (20. og 21. januar 2023) በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።

በዓሉን በስላም አስጀምሮ ላስፈጸመን ልዑል እግዚአብሔር ክብር ምሰጋና ይግባው! ከበዓሉ በረከት፣ ረድኤት ያሳትፈን! በዓሉ የበረከት፣ የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት ያድርግልን!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail

በፌስቡክ ያግኙን

Search Search

Recent Posts

  • እንኳን ለዐብይ ጾም ዘወረደ በሰላም አደረሳችሁ
  • የሀዘን መግለጫና የጸሎት መርሐ-ግብር ጥሪ
  • ፆመ ፅጌ – ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭
  • ደመራ እና ብርሃነ መስቀሉ
  • ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል

Archives

  • June 2026
  • February 2026
  • October 2025
  • September 2025
  • July 2025
  • April 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
© የኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የዘንድሮ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በድምቀት ተከበረ! Link to: የዘንድሮ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በድምቀት ተከበረ! የዘንድሮ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ... Link to: የመንፈሳዊ ትምህርትና ስብከት መርሃ ግብር በመጋቤ ሐዲስ ነቅዓጥበብ ከፍያለው Link to: የመንፈሳዊ ትምህርትና ስብከት መርሃ ግብር በመጋቤ ሐዲስ ነቅዓጥበብ ከፍያለው የመንፈሳዊ ትምህርትና ስብከት መርሃ ግብር በመጋቤ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top