በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • አገልግሎቶች
    • መርሐ ግብር
    • የህፃናት ጥምቀት
    • የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት
    • ፍትሐት
    • ክራዮች
  • የሰንበት ት/ቤት
  • ያግኙን
  • Norwegian
  • Menu Menu

ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ ሐምሌ 5 ቀን (12. juli) በአንድ በኩል የጾመ ሐዋርያት ፋሲካ የሚከበርበት ዕለት ሲኾን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ መልካሙን የክርስትና ገድል ተጋድለው ሰማዕትነት የተቀበሉበትን ቀን በታላቅና በተለየ ሁኔታ ይከበራል። ቅዱሳኑ ሰማዕታትን የተቀበሉበት ቀን የተለያየ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያናችን በዓሉን በአንድ ቀን ታከብራለች።

ክርስትናን በማስፋፋት ከፍተኛውን ሚና የተጫወቱት እነዚህ ቅዱሳን አባቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መልእክታትን ጽፈዋል። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ስምንት ምዕራፎችን የያዘ ሁለት መልእክታትን ሲጽፍ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ አንድ መቶ ምዕራፎችን የያዘ አሥራ-አራት መልእክታትን ጽፏል።

ለአግልግሎት የጠራቸውም የክብር ባለቤት የሆነው አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት የተመረጠው ጌታችን በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ሆኖ ዓሣ ለማጥመድ መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፤ ወደ እነርሱም ቀርቦ “በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ” አላቸው፡፡ ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት፡፡ (ማቴ.፬፥፲፰‐፳)። በአንጻሩ የቅዱስ ጳውሎስ አመራረጥ ደግሞ በተአምር ነው የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 9: 1 – 20፡፡

የቅዱሳኑ በረከት ዘወትር ከእኛ ጋር ይሁን አሜን!
ቅዱሳን ሐዋርያት ያቆዩልንን የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ጠብቀን፣ በክርስቲያናዊ ምግባር ጸንተን እንድንኖር፤ በመጨረሻም የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ እንድንበቃ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://lidetalemariam.no/a/wp-content/uploads/Petros-we-Paulos.jpg 549 434 webadmin@lidetalemariam.no https://lidetalemariam.no/a/wp-content/uploads/lm-logo.svg webadmin@lidetalemariam.no2024-07-11 13:45:132024-07-11 13:55:01ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ

በፌስቡክ ያግኙን

Search Search

Recent Posts

  • እንኳን ለዐብይ ጾም ዘወረደ በሰላም አደረሳችሁ
  • የሀዘን መግለጫና የጸሎት መርሐ-ግብር ጥሪ
  • ፆመ ፅጌ – ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭
  • ደመራ እና ብርሃነ መስቀሉ
  • ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል

Archives

  • June 2026
  • February 2026
  • October 2025
  • September 2025
  • July 2025
  • April 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
© የኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: እንኩዋን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሳችሁ! Link to: እንኩዋን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሳችሁ! እንኩዋን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሳ... Link to: እንኳን ለአብርሃሙ ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ! Link to: እንኳን ለአብርሃሙ ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ! እንኳን ለአብርሃሙ ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top