በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • አገልግሎቶች
    • መርሐ ግብር
    • የህፃናት ጥምቀት
    • የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት
    • ፍትሐት
    • ክራዮች
  • የሰንበት ት/ቤት
  • ያግኙን
  • Norwegian
  • Menu Menu

የዐብይ ጾም ሁለተኛው ሰንበት “ቅድስት”

የዐቢይ ጾም ሁለተኛው ሰንበት ኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ እንደሰየመው “ቅድሰት” ይባላል። ቅድስት ማለት ልዩ፣ ጽኑዕ፣ ክቡር ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን በባሕርዩ ቅዱስ ነው፡፡ ስለሆነም በመልኩና በምሳሌው አክብሮ የፈጠረንን እኛም ቅዱሳን እንድንሆን ይፈለጋል፡፡ “ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ” 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:15-16፡፡ ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፣ ይሰበካል። ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱንና ሳምንቱን ስለ ቅድስና ታስተምራለች፡፡ ይህንን በተመለከተ በዶ/ር ቀሲስ ዘበነ ለማ ከዚህ በፊት የተሰጠውን ትምህርት ከዚህ በታች ያለውን ቪዲዮ ይመልከቱ።

የዕለቱ ምስባክ “እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ። ምስጋናና ውበት በፊቱ፥ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።” መዝ 96:5-6

የዕለቱ ወንጌል “ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።” የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 6: 16

 

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://lidetalemariam.no/a/wp-content/uploads/Kidist.jpg 213 250 webadmin@lidetalemariam.no https://lidetalemariam.no/a/wp-content/uploads/lm-logo.svg webadmin@lidetalemariam.no2024-03-15 21:26:442024-03-16 17:04:34የዐብይ ጾም ሁለተኛው ሰንበት “ቅድስት”

በፌስቡክ ያግኙን

Search Search

Recent Posts

  • እንኳን ለዐብይ ጾም ዘወረደ በሰላም አደረሳችሁ
  • የሀዘን መግለጫና የጸሎት መርሐ-ግብር ጥሪ
  • ፆመ ፅጌ – ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭
  • ደመራ እና ብርሃነ መስቀሉ
  • ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል

Archives

  • June 2026
  • February 2026
  • October 2025
  • September 2025
  • July 2025
  • April 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
© የኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: እንኳን ለታላቁ ዐብይ ጾም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ! Link to: እንኳን ለታላቁ ዐብይ ጾም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ! እንኳን ለታላቁ ዐብይ ጾም በሰላምና በጤና አደ... Link to: “ምኩራብ” የዐቢይ ጾም 3ኛ ሳምንት Link to: “ምኩራብ” የዐቢይ ጾም 3ኛ ሳምንት “ምኩራብ” የዐቢይ ጾም 3ኛ ሳምንት
Scroll to top Scroll to top Scroll to top