በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • አገልግሎቶች
    • መርሐ ግብር
    • የህፃናት ጥምቀት
    • የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት
    • ፍትሐት
    • ክራዮች
  • የሰንበት ት/ቤት
  • ያግኙን
  • Norwegian
  • Menu Menu

የዘንድሮ 2017 ዓ/ም ጾመ ነነዌ!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዘንድሮን የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ መግለጫ ሙሉ መልእክት እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡ፡፡
የዘንድሮ የነነዌ ጾም ከነገ የካቲት 03 ቀን 2017 (fra 10. febryar 2025) ጀምሮ ይጾማል። ሦስት ቀናት የሚጾመው ይህ ጾም የነነዌን ሕዝብ ከጥፋት መመለስ፣ የእግዚአብሔርን ምሕረት እንዲሁም የነቢዩ ዮናስን የዋህነት ያስረዳናል፡፡

የነነዌ ከተማ አስቀድሞ በአሦር አማካይነት ከጤግሮስ ወንዝ በስተምሥራቅ (በአሁኗ ኢራቅ ሞሱል ከተማ አቅራቢያ) ተመሠረተች (ዘፍ 10፡11-12)፡፡ ከብዙ ዘመናት በኋላ የንጉሥ ሰናክሬም መቀመጫ ሆነች (2ኛ ነገ 19፡36)፡፡ በዚያን ዘመን ነነዌ በአካባቢው ካሉት ታላላቅ ከተሞች አንዷ ነበረች፡፡

በዚያን ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ክፋታቸው ከእግዚብሔር ዘንድ ደርሶ ስለነበር እግዚአብሔር ነቢዩ ዮናስን ወደዚያ ላከው፡፡ “ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ ክፉታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቶአልና በእርስዋ ላይ ስበክ።” ብሎ ላከው፡፡ ዮናስ ግን ወደ ተርሴስ ለመኮብለል ቢሞክርም እግዚአብሔር በድንቅ ተአምራቱ ወደ ነነነዌ መልሶታል፡፡ እንደገናም እግዚአብሄር ለዮናስ “ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ የምነግርህንም ስብከት ስበክላት አለው።” ዮናስም ሄዶ “ነነዌ በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች!” ብሎ ጮኸ፣ ሰበከ!

የነነዌ ሰዎችም ፈጥነው ንስሐ ገቡ፡፡ “የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ። ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ።” እግዚአብሔርም ምህረቱን ላከላቸው፡፡ “እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም።” በዚህ ዘመን ፈጥነው ንስሐ በመግባታቸው ከጥፋት ድነዋል፡፡ ሙሉ ታሪኩን በትንቢተ ዮናስ ከምዕራፍ 1 እስከ 4 ላይ ይገኛል።

ስለዚህ የነነዌ ታሪክ የጾምን እና የንሰሃን ፍጹም ኃይል እና ዋጋ የሚያስተምረን ነውና ይህንኑ እያሰብን ጾመን እንድንጠቀም የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን አማላጅነት፣ የቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ እንዲሁም በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን! የሃገራችንንና የቤተ ክርስቲያናችንን ሰላምና አንድነት ይጠብቅልን!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://lidetalemariam.no/a/wp-content/uploads/Propheten-Yonas.jpg 260 458 webadmin@lidetalemariam.no https://lidetalemariam.no/a/wp-content/uploads/lm-logo.svg webadmin@lidetalemariam.no2025-02-09 17:58:272025-02-09 19:33:17የዘንድሮ 2017 ዓ/ም ጾመ ነነዌ!

በፌስቡክ ያግኙን

Search Search

Recent Posts

  • እንኳን ለዐብይ ጾም ዘወረደ በሰላም አደረሳችሁ
  • የሀዘን መግለጫና የጸሎት መርሐ-ግብር ጥሪ
  • ፆመ ፅጌ – ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭
  • ደመራ እና ብርሃነ መስቀሉ
  • ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል

Archives

  • June 2026
  • February 2026
  • October 2025
  • September 2025
  • July 2025
  • April 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
© የኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የዘንድሮ 2017 ዓ/ም የጥምቀት በዓል ቅዳሜ ጥር 10 እና ዕሑድ ጥር 11 ቀን 2017 ዓ/ም (18. og 19. januar 2025) በበርገን መንበረ ልዑል ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ትክብሮ ይውላል! Link to: የዘንድሮ 2017 ዓ/ም የጥምቀት በዓል ቅዳሜ ጥር 10 እና ዕሑድ ጥር 11 ቀን 2017 ዓ/ም (18. og 19. januar 2025) በበርገን መንበረ ልዑል ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ትክብሮ ይውላል! የዘንድሮ 2017 ዓ/ም የጥምቀት በዓል ቅዳሜ ጥር 10 እና... Link to: ኒቆዲሞስ (የዐብይ ጾም ፯ኛ ሳምንት) Link to: ኒቆዲሞስ (የዐብይ ጾም ፯ኛ ሳምንት) ኒቆዲሞስ (የዐብይ ጾም ፯ኛ ሳምንት)
Scroll to top Scroll to top Scroll to top