በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • አገልግሎቶች
    • መርሐ ግብር
    • የህፃናት ጥምቀት
    • የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት
    • ፍትሐት
    • ክራዮች
  • የሰንበት ት/ቤት
  • ያግኙን
  • Norwegian
  • Menu Menu

የዘንድሮ 2017 ዓ/ም የጥምቀት በዓል ቅዳሜ ጥር 10 እና ዕሑድ ጥር 11 ቀን 2017 ዓ/ም (18. og 19. januar 2025) በበርገን መንበረ ልዑል ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ትክብሮ ይውላል!

የጥምቀት በዓል ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ በማየ ዮርዳኖስ መጠመቁን ለመዘከር የሚከበር በዓል ነዉ፡፡ ጥምቀት ከእግዚአብሔር ዳግም የምንወለድበት፣የቤተ ክርስቲያን አባል የምንሆንበት፣ የኃጢያት ስርየትና የስጋ ፈውስ የምናገኝበት፣ ነጻነታችን የታወጀበት፣ የዕዳ ደብዳቤአችን የተቀደደበት፣ የባርነት ቀንበር የተሰበረበት፣ ምስጢረ ሥላሴ የተገለጠበት ረቂቅ ምስጢር ነው።

ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀትን የመሠረተው በሦስት መንገድ ነው።

መጀመሪያ በተግባር ራሱ ተጠምቆ እንድንጠመቅ አስተምሮናል፤ አርአያም ሆኖናል (ማቴ 3፡13)፡፡

ሁለተኛም በትምህርቱ “ያመነ የተጠመቀ ይድናል” (ማር 16፡16):: እንዲሁም “እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔር መንግሥት ሊያይ አይችልም” (ዮሐ 3፡3-6) በማለት ጥምቀት ለድኅነት አስፈላጊ መሆኑን አስተምሯል፡፡

ሦስተኛም ለቅዱሳን ሐዋርያት በሰጣቸው ትዕዛዝ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” (ማቴ 28፡19-20) በማለት ምስጢረ ጥምቀትን መስርቶልናል። ይህንንም መሠረት በማድረግ ሃይማኖታቸው የቀና ቅዱሳን አባቶች “ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኀጢአት፣ ኀጢአትን በምታስተሠርይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን” በማለት መሠረተ እምነትን ደንግገዋል፡፡

የዘንድሮ 2017 ዓ/ም የጥምቀት በዓል እንደወትሮው በኖርዌይ ውስጥ በሚገኙ ትላልቅ አድባራት ማለትም
– የበርገን መንበረ ልዑል ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ
– የስታቫንገር ደብረ ገነት መድሃኔ አለም ወኪዳነ ምህረት ቤ/ክ
– የኦስሎ ማህደረስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ
– የክርስቲያንሳንድ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ
-የትሮንድሐይም ምስራቀ ጸሃይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ታቦታት በጋራ በተሳተፉበት በበርገን መንበረ ልዑል ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ አዘጋጅነት በበርገን ከተማ (Vilhelm Bjerknes vei 24, 5081 Bergen) ቅዳሜና ዕሑድ ጥር 10 እና 11 ቀን 2017 ዓ/ም (18. og 19. januar 2025) በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ይውላል።

በዓሉን በስላም አስጀምሮ እንዲያስፈጽመን የልዑል እግዚአብሔር ችርነት አይለየን! ከበዓሉ በረከት፣ ረድኤት ያሳትፈን! በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት ያድርግልን!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://lidetalemariam.no/a/wp-content/uploads/Bergen1-1.jpg 384 271 webadmin@lidetalemariam.no https://lidetalemariam.no/a/wp-content/uploads/lm-logo.svg webadmin@lidetalemariam.no2025-01-16 23:24:352025-01-16 23:41:09የዘንድሮ 2017 ዓ/ም የጥምቀት በዓል ቅዳሜ ጥር 10 እና ዕሑድ ጥር 11 ቀን 2017 ዓ/ም (18. og 19. januar 2025) በበርገን መንበረ ልዑል ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ትክብሮ ይውላል!

በፌስቡክ ያግኙን

Search Search

Recent Posts

  • እንኳን ለዐብይ ጾም ዘወረደ በሰላም አደረሳችሁ
  • የሀዘን መግለጫና የጸሎት መርሐ-ግብር ጥሪ
  • ፆመ ፅጌ – ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭
  • ደመራ እና ብርሃነ መስቀሉ
  • ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል

Archives

  • June 2026
  • February 2026
  • October 2025
  • September 2025
  • July 2025
  • April 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
© የኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! Link to: እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ... Link to: የዘንድሮ 2017 ዓ/ም ጾመ ነነዌ! Link to: የዘንድሮ 2017 ዓ/ም ጾመ ነነዌ! የዘንድሮ 2017 ዓ/ም ጾመ ነነዌ!
Scroll to top Scroll to top Scroll to top