የማሀደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ ከ 2025 – 2030 የአምስት ዓመት መሪ ዕቅድ

የማሀደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ ከ 2025 – 2030 የአምስት ዓመት መሪ ዕቅድ የተዘጋጀውን ረቂቅ ማብራሪያ በመስጠት ከቤተ ክርስቲያኒቱ ምዕመናን እና ምዕመናት ጋር በዛሬ ዕለት ዕሑድ ጥቅምት 10 ቀን ከሰንበት ቀዳሴ ሥነ ስርዓት በኋላ ዉይይት ተደርጓል፡፡ በዚሁም መሰረት የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው መልስ የተሰጠባቸው ሲሆን ለመሪ ዕቅዱ እንደግብአት የሚጠቅሙ ሃሳቦችም ተሰንዝረዋል።
ይህ የአምስት ዓመት መሪ እቅድ የተዘጋጀው ከሰበካ ጉባኤው የተወከሉ ሁለት አባላት “ከአጥቢያ ዶት ኮም” ጋር በመተባበር ሲሆን ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ማብራሪያ እና ውይይት ከሰበካ ጉባኤው ጋር ያደረጉ መሆኑን እና ለመሪ እቅዱ የሚጠቅሙ ጠቃሚ ግብአቶች እንደተገኙ ተገልጿል። በተመሳሳይ ሁኔታ በሚቀጥሉት ሳምንታትም በአካባቢው ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እና ሃገርስብከት ጋር ውይይት ለማድረግ ሃሳብ እንዳለ በተጨማሪ ተግልጿል።