በዲያቆን ጎርጎርዮስ ደጀኔ ለወጣቶች የሚሰጠው ትምህርት በመቀጠል ዛሬ ቅዳሜ 01. juni ከ16 ሰዓት ጀምሮ እና ነገ ከቅዳሴ በኋላ የመጨረሻው ትምህርት በቤተ ክርስቲያናችን ይካሄዳል።
ዲያቆን ጎርጎርዮስ ደጀኔ ከአሜሪካ መጥቶ ለወጣቶች የተዘጋጀውን የመጀመሪያውን ጉባኤ ባለፈው ሳምንት ማድረጉ ይታወሳል። እጅግ ብዙ ወጣቶች በቤተክርስቲያን ተገኝተው ትምህርት ሲማሩ ሰንብተዋል። ዲያቆን ጎርጎርዮስ ዛሬ ቅዳሜ 01. juni ከ16 ሰዓት ጀምሮ እና ነገ ከቅዳሴ በኋላ የመጨረሻ ትምህርት አስተምሮ ወደ መጣበት ይመለሳል። የምትችሉ ሁላችሁ በመገኘት ትምህርቱን እንድትከታተሉ በእግዚአብሔር ስም ጥሪ እናስተላልፋለን።