በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • አገልግሎቶች
    • መርሐ ግብር
    • የህፃናት ጥምቀት
    • የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት
    • ፍትሐት
    • ክራዮች
  • የሰንበት ት/ቤት
  • ያግኙን
  • Norwegian
  • Menu Menu

የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ ለሐዋርያቱ በተለያየ ጊዜ እየተገለጠ ለአገልግሎት ሲያዘጋጃቸው እና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ምስጢር እያስተማራቸው ከቆየ በኋላ በ40ኛው ቀን በሐዋርያቱ ፊት አርጓል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው የጌታችን አበይት በዓላት አንዱ ዕርገት ነው። የዘንድሮ የእርገት በዓል ሓሙስ ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ/ም (13. juni 2024) ቢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ተከብሮ እልፏል።

በዓለ ዕርገት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ በታላቅ መንፈሳዊ ክብር ከሚከበሩት በዓላት አንዱ ነው፡፡ በዓሉ የሚውለው ዕለተ ሐሙስን ሳይለቅ ከበዓለ ትንሣኤ አርባኛው ቀን ላይ ነው። ቅዱስ ሉቃስ በሐዋርያት ሥራ ላይ “ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው” ሐዋ. 1:3 በማለት የጻፈውን መሠረት በማድረግ ነው፡፡

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ  ዕርገቱ በምድር ላይ የሚሠራውን የትሕትና ሥራ የመፈጸሙ ምልክት ነው፡፡ ዕርገቱም ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት “በዕልልታና በመለከት ድምፅ ላረገ ለአምላካችን፣ ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና አቅርቡ” መዝ 46፥5፡ እንዳለው በታላቅ ክብር እልልታና ምስጋና ነው፡፡

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://lidetalemariam.no/a/wp-content/uploads/Erget1.jpg 270 187 webadmin@lidetalemariam.no https://lidetalemariam.no/a/wp-content/uploads/lm-logo.svg webadmin@lidetalemariam.no2024-06-18 21:48:082024-06-18 21:48:08የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት

በፌስቡክ ያግኙን

Search Search

Recent Posts

  • የሀዘን መግለጫና የጸሎት መርሐ-ግብር ጥሪ
  • ፆመ ፅጌ – ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭
  • ደመራ እና ብርሃነ መስቀሉ
  • ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል
  • ጸሎት

Archives

  • February 2026
  • October 2025
  • September 2025
  • July 2025
  • April 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
© የኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በዲያቆን ጎርጎርዮስ ደጀኔ ለወጣቶች የሚሰጠው ትምህርት በመቀጠል ዛሬ ቅዳሜ 01. juni ከ16 ሰዓት ጀምሮ እና ነገ ከቅዳሴ በኋላ የመጨረሻው ትምህርት በቤት ክርስቲያናችን ይሰጣሉ። Link to: በዲያቆን ጎርጎርዮስ ደጀኔ ለወጣቶች የሚሰጠው ትምህርት በመቀጠል ዛሬ ቅዳሜ 01. juni ከ16 ሰዓት ጀምሮ እና ነገ ከቅዳሴ በኋላ የመጨረሻው ትምህርት በቤት ክርስቲያናችን ይሰጣሉ። በዲያቆን ጎርጎርዮስ ደጀኔ ለወጣቶች የሚሰጠው... Link to: ዓመታዊው የሰንበት ትምህርት ቤት የመዝጊያ መርሃግብርና የወላጆች የትውውቅ ሥነ ሥርዓት Link to: ዓመታዊው የሰንበት ትምህርት ቤት የመዝጊያ መርሃግብርና የወላጆች የትውውቅ ሥነ ሥርዓት ዓመታዊው የሰንበት ትምህርት ቤት የመዝጊያ መርሃግብርና...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top