እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።” መዝ. 33፡7

ይህ ጥቅስ የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሰዎች ከእግዚአብሔር ተልኮ በዙሪያቸው ሆኖ ከመከራ እንደሚያድናቸው ያስተምራል፡፡

ታህሣስ 19 ቀን በዚህ ቀን የእግዚአብሔር ሰዎች፣ የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች የነበሩት ወጣቶች ሰለስቱ ደቂቅ አናንያ (ሲድራቅ) ፤ አዛርያ (ሚሣቅ) ፤ ሚሣኤል (አብድናጎ) ንጉሱ ናቡከደነጽዖር ላሰራው ጣዖት አንሰግድም፣ የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶኑ ሊያድነን ይችላል ብለው በዕምነታቸው ጸንተው የተገኙበት ዕለትና ቅዱስ ገብርኤል ከእሳት ያዳናቸው ዕለት መታሰቢያ በዓል በታላቅ ደስታ የሚከበርበት ቀን ነው። ሙሉ ታሪኩን በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 3 ላይ ይገኛል።

በተጨማሪም በዕለቱ እስከአሁን ሲዘጋጅ የቆየው የቤተ ክርስቲያኒቱ የ5 ዓመት (2025 – 2030) መሪ ዕቀድ ለምዕመናንና ምዕመናት ቀርቦ ይጸድቃል።

በኦስሎና አካባቢው የምትገኙ ምዕመናንና ምዕመናት በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ተገኝታችሁ በዓሉን በድምቀት በማክበር የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የደብሩ የሰባካ መንፈሳዊ አስተዳደር በማክበር ይጋብዛል።

የመልአኩ የሊቀ መላዕክት የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃው፣ ረድኤትና በረከቱ አይለየን!