እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤ/ክ በየዓመቱ መስከረም 16 ቀን (26. september) የመስቀል በዓል በዋዜማው የደመራን ችቦ በማብራት በደመቀ ሁኔታ ይከበራል፡፡ በዓሉ የንጉስ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ፣ ደመራ አስደምራ በእሳት ባቀጣጠለችው ጊዜ፣ ጢሱ ወደ ላይ ከወጣ በኋላ ተመልሶ ያረፈበትን ሥፍራ አስቆፍራ ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ማግኘቷን በማስመልከት በየዓመቱ የሚከበር ታላቅ ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓል ነው፡፡
የመስቀል በዓል አከባበር በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ የትምህርትና ባህል ማዕከል (UNESCO) መዝገብ በዓለም የመጀመሪያው የማይዳሰስና የማይጨበጥ ህሊናዊና ባህላዊ ቅርስ በመሆን ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
የዘንድሮን የደመራ በዓል ሐሙስ መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም (torsdag 26. september 2024) ከቀኑ 16 ሰዓት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያናችን ፊት ለፊት በሚገኘው የመኪና ማቆሚያ ላይ የሚከበር ስለሆነ በቦታው በመገኘት በዓሉን በአንድነትና በድምቀት እንድናከብር የደብሩ ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ በማክበር ይጋብዛል፡፡