ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የምሥራቅ ጎጃም እንዲሁም የጀርመንና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለአራት ታዳጊዎች የዲቁና ሥልጣነ ክህነትን ሰጡ !

ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የምሥራቅ ጎጃም እንዲሁም የጀርመንና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት የካቲት 10 ቀን 2016 ዓ/ም በደብራችን በመገኘት በመላዋ ኖርዌይ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ለሚያገለግሉ አራት ደቀ መዛሙርት የዲቁና ሥልጣነ ክህነት ሰጥተዋል።
በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ኤልያስ መልካም ፈቃድ የአብነት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩት አራት ደቀ መዛሙርት የዲቁና ሥልጣነ ክህነት በሰጡበት ወቅት ለአገልጋዮቹ በሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ትምህርት አስተምረው በዓለም ዙሪያ ያለችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በቅንነትና በእውቀት እንዲያገለግሏትም አባታዊ መመሪያም አስተላልፈዋል። ለተመሳሳይ መረጃ የሚከተሉትን ሊንኮች በመጫን ይመልከቱ።