የእመቤታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ዓመታዊ የንግስ ክብረ በዓል በቤተ ክርስቲያናችን በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሰረት በየዓመቱ የካቲት 16 ቀን የቅድስተ ቅዱሳን የድንግል ማርያም ዓመታዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል በታላቅ ድምቀት ይከበራል ። እመቤታችን ከጌታችን መቃብር በመሄድ ልጄ ወዳጄ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መትተህ ልምናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ በአለች ጊዜ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቁ ጌታችንም እልፍ ከእልፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ለኪ ማርያም ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት፡፡ እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጻውን መባዕ የሰጠውን ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡ ጌታችንም ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበ አቡየ ሕያው ወበመንፈስ ቅዱስ ብሎ ቃል ገብቶላት አርጓል፡፡ ስለዚህ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን ከመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የምሕረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ቀን እና የቃል ኪዳን ፍጻሜ የተከናወነበት ዕለት ሰለሆነ በታላቅ ድምቀት ይከበራል። ርዕሰ ኪዳናትም ይባላል። ቅዱሳት መጻሀፍት ታሪክ እንደምንማረው በብለይኪዳን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ከቅዱሳን ወዳጆቹ የፈጸማቸው አምሰት ልዩ ልዩ ኪዳናት ተከናውነዋል እነዚህም
1- ኪዳነ አዳም: አዳም ሕግን በመጣሱ በሰራው ጥፋት እያዘነ ፈጣሪውን ይቅርታ ቢጠይቅ ከአምስተ ቀን ተኩል በኃላ ከልጅልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው የምህረት ተስፋን ሰጠው። ዘመኑም ሲደርስ የአዳም ተስፋ ከሆነች ከቅድስተ ቅዱሳን ከድንግል ማርያም እግዚአብሔር ወልድ በቤተልሔም ተወለደ ዓለሙንም አዳነ ።
2- ኪዳነ ኖኅ: ምደርቱንም ዳግመኛ በንፍር ውኃ እንደማያጠፋት በስሙ ማለለት ይህም እስከዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል። ዘፍ 9፥8-17
3- ኪዳነ አበርሃም: አብርሃም አባታችን ከሚኖርበት ሀገሩን ቤተሰቡን ትቶ እንዲወጣ ከእግዚአብሔር ቢታዘዝ እርሱም ፈቃደኛ በመሆን ወደ ማያውቀውሀገርሲሰደድበልቡየታመነውከአምለኩየተቀበለውየተስፋቃልኪዳንይዞነበር።የቃልኪዳንምልክቱም<<ከእናንተወንድሁሉይገረዝየቍልፈታችሁንም ሥጋ ትገረዛላችሁ በእኔ እና በእናንተመካካልላለው ቃል ኪዳንምልከክት ይሆናል ።–ቃል ኪዳኔም በሥጋችሁ የዘላላም ቃል ኪዳን ይሆናል ።>>በማለት አብርሃምን ከወገኖቹ ጋር የእግዚአብሔር ሕዝብ ለርስቱ የተለየ የተመረጠ እንዲሆኑ አድርጓል።
4- ኪዳነ ሙሴ: ይህ ኪዳን ለሊቀ ነቢያት ሙሴ የተሰጠ ሲሆን ሕዝቡትዕዛዘ እግዚአብሔርን እንዲጠብቁ እና ከእርሱ ሌላ አምላክ እናዳያመልኩ መመሪያ ይሆናቸው ዘንድ በነብዪ አማካኝነት የመጀመሪያቱን ጽላት በመስጠት ቃል ኪዳኑን አጽንቷል። ዘጸ24፥1-20
5- ኪዳነ ዳዊት: ይህ ኪዳን በብሉይ ኪዳን ከተፈጸሙት ዐበይት ኪዳናት አንዱ ሲሆን ከእረኝነት አንስቶ የመረጠው እግዚአብሔር በታናሽነቱ ህዝበ እስራኤልን ይመራ ዘንድ የመረጠው በትረ መንግሥትን ከቤቱ ለዘላዓለም እንዳማይጠፋ ቃል ኪዳን ገብቶለታል መዝ131፥11-13
በዓሉ በዕለተ ቀኗ ቅዳሜ የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ/ም (24. februar 2023) ከጠዋቱ 07:00 ሰዓት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያናችን በቅዳሴ፣ በስብከትና በመዝሙር በደማቅ ሁኔታ ተክብሮ አልፏል ።
ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት ከሁላችን ጋር ይሁን! ድንግል ማርያም በቃል ኪዳኗ አትለየን!