ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች
በአባልነት ለመመዝገብ የምትፈልጉ የአባልነት ፎርምና ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት
የባንክ ሂሳብ ቁጥር፡ 1503 622 909
111030
በቋሚነት
በቋሚነት በየወሩ በቀጥታ በባንክ አካውንት ወይንም በቪፕስ ለመክፈል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ የማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ በጥቂት ግለሰቦች አነሳሽነትና በእግዚአብሔር ፈቃድ መጋቢት 6 ቀን 2007 ዓ/ም ተመሠረተ፡፡ በወቅቱ የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ እንጦስ በቦታው ተገኝተው ቤተ ክርስቲያኑን ባርከውና ቀድሰው መሠረት ከመጣላቸውም በላይ በቀጣይነት ከአንድ ዓመት በኋላ የሊቀ መላኩን የቅዱስ ገብርኤል ጽላት በማስመጣት ለቤ/ክርስቲያኑ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ሲመሰረት 19 ምዕመናንና ምዕመናት በአባልነት ተመዝግበው የነበሩት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የአባላት ቁጥር ከ200 በላይ ሆኗል፡፡ ቋሚ ቤ/ክ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ለጊዜው በኪራይ ቀደም ሲል በካምፐን ሜኒሄትስ ሁስና በካምፐን ሺርከ አሁን ደግሞ በCaspar Storms vei 12, 0664 Oslo, የሰንበት ቅዳሴ፣ የሰንበት ት/ቤትና እንዲሁም የበዓላት መርሃ ግብር ሳይታጎሉ ቤተ ክርስቲያኑ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ ያልተቋረጠ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
ፎቶ፦ ብጹዕ አቡነ እንጦስ ቤተክርስቲያናችህንን ባርከው አገልግሎት ሲያስጀምሩ
“ምኩራብ” የዐቢይ ጾም 3ኛ ሳምንት
የዐቢይ ጾም 3ኛ ሳምንት ስያሜ “ምኩራብ” ይባላል። “ምኩራብ” ማለትም ቀጥተኛ ፍችው ኮረብታ፣ ተራራ የሚያኸል ታላቅ ሕንጻ ማለት ሲሆን ከዚህም የተነሣ የአይሁድ ቤተ ጸሎት ምኩራብ በመባል ይታወቃል። ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ እየገባ ለማስተማሩና በምኩራብ የሚሸጡ የሚለውጡ ነጋዴዎችን ለማስወጣቱ፣ ቤተ መቅደሱን ለማስከበሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ስያሜ ነው።
የዐብይ ጾም ሁለተኛው ሰንበት “ቅድስት”
የዐቢይ ጾም ሁለተኛው ሰንበት ኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ እንደሰየመው “ቅድሰት” ይባላል። ቅድስት ማለት ልዩ፣ ጽኑዕ፣ ክቡር ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን በባሕርዩ ቅዱስ ነው፡፡ ስለሆነም በመልኩና በምሳሌው አክብሮ የፈጠረንን እኛም ቅዱሳን እንድንሆን ይፈለጋል፡፡
“ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ” 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:15-16
እንኳን ለታላቁ ዐብይ ጾም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!
በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚገኙት 8 ሣምንታት ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ እንደሰየመው የየራሳቸው የሆነ ስያሜና ትርጉም አላቸው። በዚሁም መሰረት የዓቢይ ጾም መግቢያ የሆነው የመጀመሪያው እሁድና ከእርሱ ጋር ተያይዞ ያለው የሚቀጥለው ሳምንት “ዘወረደ” ይባላል፡፡
“ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው። የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 3:13”
ጾመ ነነዌ!
የዘንድሮ የነነዌ ጾም ከነገ የካቲት 18 ቀን 2016 (fra 16. febryar 2016) ጀምሮ ይጾማል። ሦስት ቀናት የሚጾመው ይህ ጾም የነነዌን ሕዝብ ከጥፋት መመለስ፣ የእግዚአብሔርን ምሕረት እንዲሁም የነቢዩ ዮናስን የዋህነት ያስረዳናል፡፡ ስለዚህ የነነዌ ታሪክ የጾምን እና የንሰሃን ፍጹም ኃይል እና ዋጋ የሚያስተምረን ነውና ይህንኑ እያሰብን ጾመን እንድንጠቀም የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን አማላጅነት፣ የቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን! የሃገራችንንና የቤተ ክርስቲያናችንን ሰላምና አንድነት ይጠብቅልን!
የእመቤታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ዓመታዊ የንግስ ክብረ በዓል በቤተ ክርስቲያናችን በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሰረት በየዓመቱ የካቲት 16 ቀን የቅድስተ ቅዱሳን የድንግል ማርያም ዓመታዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል ሲሆን በዓሉም ከ33ቱ በዓላት አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን ከመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የምሕረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ቀን እና የቃል ኪዳን ፍጻሜ የተከናወነበት ዕለት ሰለሆነ በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በዛሬው ዕለት በደብራችን እና በመላው ኖርዌይ ለሚያገለግሉ አራት ደቀ መዛሙርት የዲቁና ሥልጣነ ክህነትን ሰጡ።
ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የምሥራቅ ጎጃም እንዲሁም የጀርመንና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት የካቲት 10 ቀን 2016 ዓ/ም በደብራችን ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን በመገኘት በመላዋ ኖርዌይ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ለሚያገለግሉ አራት ደቀ መዛሙርት የዲቁና ሥልጣነ ክህነት ሰጥተዋል።
ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በነገው ዕለት በደብራችን ተገኝተው በኖርዌይ ተወልደው፣ ተምረው ደቀ መዛሙርት ለሚሆኑ ልጆቻችን ሥልጣነ ክህነትን ይሰጣሉ።
በነገው ዕለት የካቲት 10 ቀን 2016 ዓ/ም (18. februar 2024) አባታችን ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በኢ.ኦ.ተ.ቤ. የምስራቅ ጎጃም እንዲሁም የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ በደብራችን በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው በኖርዌይ ሃገር ተወልደው፣ ተምረው ለዲቁና ለደረሱ ደቀ መዛሙርት ለሚሆኑ ልጆቻችን ሥልጣነ ክህነትን ይሰጣሉ።
እንኳን ለዘንድሮ አስተርእዮ ማርያም ክብረ በዓል አደረሳችሁ!!!
“ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአፅብ ለኩሉ” “ሞት ለሟች ይገባል የማርያም ሞት ግን ለሁሉ ይደንቃል!!!”
ጥር 21 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕረፍት ይታሰባል፡፡
በዓሉን በማስመልከት ነገ ማክሰኞ ጥር 21 ቀን 2024 ዓ/ም (30. januar 2023) ከጠዋቱ 07:30 ሰዓት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያናችን የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ይካሄዳል። በኦስሎና አካባቢው የምትገኙ ምዕመናንና ምዕመናት በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ተገኝታችሁ በዓሉን በድምቀት በማክበር የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የደብሩ የሰባካ መንፈሳዊ አስተዳደር በማክበር ይጋብዛል።
የመንፈሳዊ ትምህርትና ስብከት መርሃ ግብር በመጋቤ ሐዲስ ነቅዓጥበብ ከፍያለው
በስታቫንገር ደብረ ገነት መድሃኔ አለም ወኪዳነ ምህረት ቤ/ክ የተከበረውን የዘንድሮ የጥምቀት በዓል ላይ ከኢትዮጵያ ተጋብዘው የተገኙት መምህር መጋቤ ሐዲስ ነቅዓ ጥበብ ከፍ ያለው በነገው ዕለት ዕሑድ ጥር 19 ቀን 2016 ዓ/ም (søndag 28. januar 2023) በደብራችን ማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ ተገኝተው ጥልቅ መንፈሳዊ ትምህርታቸን ያስተምሩናል።
የጌታችን የመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በስታቫንገር ከተማ በድምቀት ተከብሮ ዋለ!
የጥምቀት በዓል ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ በማየ ዮርዳኖስ መጠመቁን ለመዘከር የሚከበር በዓል ነዉ፡፡ ጥምቀት ከእግዚአብሔር ዳግም የምንወለድበት፣የቤተ ክርስቲያን አባል የምንሆንበት፣ የኃጢያት ስርየትና የስጋ ፈውስ የምናገኝበት፣ ነጻነታችን የታወጀበት፣ የዕዳ ደብዳቤአችን የተቀደደበት፣ የባርነት ቀንበር የተሰበረበት፣ ምስጢረ ሥላሴ የተገለጠበት ረቂቅ ምስጢር ነው።