ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች
በአባልነት ለመመዝገብ የምትፈልጉ የአባልነት ፎርምና ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት
የባንክ ሂሳብ ቁጥር፡ 1503 622 909
111030
በቋሚነት
በቋሚነት በየወሩ በቀጥታ በባንክ አካውንት ወይንም በቪፕስ ለመክፈል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ የማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ በጥቂት ግለሰቦች አነሳሽነትና በእግዚአብሔር ፈቃድ መጋቢት 6 ቀን 2007 ዓ/ም ተመሠረተ፡፡ በወቅቱ የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ እንጦስ በቦታው ተገኝተው ቤተ ክርስቲያኑን ባርከውና ቀድሰው መሠረት ከመጣላቸውም በላይ በቀጣይነት ከአንድ ዓመት በኋላ የሊቀ መላኩን የቅዱስ ገብርኤል ጽላት በማስመጣት ለቤ/ክርስቲያኑ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ሲመሰረት 19 ምዕመናንና ምዕመናት በአባልነት ተመዝግበው የነበሩት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የአባላት ቁጥር ከ200 በላይ ሆኗል፡፡ ቋሚ ቤ/ክ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ለጊዜው በኪራይ ቀደም ሲል በካምፐን ሜኒሄትስ ሁስና በካምፐን ሺርከ አሁን ደግሞ በCaspar Storms vei 12, 0664 Oslo, የሰንበት ቅዳሴ፣ የሰንበት ት/ቤትና እንዲሁም የበዓላት መርሃ ግብር ሳይታጎሉ ቤተ ክርስቲያኑ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ ያልተቋረጠ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
ፎቶ፦ ብጹዕ አቡነ እንጦስ ቤተክርስቲያናችህንን ባርከው አገልግሎት ሲያስጀምሩ
የዕመቤታችን ቅድስትድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በድምቀት ተከብሮ ዋለ
የዕመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል ሐሙስ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ/ም (torsdag 09. mai 2024) በታላቅ ድምቀት ከኢትዮጵያ፣ ካውሮፓና ከኖርዌይ የተጋበዙ መምህራን፣ ቀሳውስትና መዘምራን በተገኙበት በማህሌት፣ በመዝሙር፣ በቅዳሴና ታቦተ ንግስ ተከብሮ ዋለ።
ግንቦት 1 ቀን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል
የዘንድሮ 2016 ዓ/ም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በቤተ ክርስቲያናችን በዕለተ ቀኗ በመጪው ሐሙስ ግንቦት 1 ቀን ከኢትዮጵያ፣ ካውሮፓና ከኖርዌይ የተጋበዙ መምህራን፣ ቀሳውስትና መዘምራን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት በማህሌት፣ በመዝሙር፣ በቅዳሴና ታቦተ ንግስ ከውዜማው ጀምሮ ይከበራል።
ቤተ ክርስቲያኑ ከዋዜማው ረቡዕ ሚያዚያ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ከምሽቱ 20:00 ሰዓት ጀምሮ ከኢትዮጵያ በሚመጡት መምህር መጋቤ ሐዲስ ነቅዓጥበብ ከፍያለው በትምህርትና ስብከተ ወንጌል ተጀምሮ የማህሌት፣ የመዝሙር፣ የቅዳሴና ታቦተ ንግስ መርሃ ግብሩ በተከታታይ እስከ ሚቀጥለው ግንቦት 1 ቀን ድረስ ይከናወናል።
እንኳን ለ2016 ዓ/ም የጌታችንና የመድሃንታችን የእየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድኅነተ ዓለምን በመስቀል ላይ ከፈጸመ በኋላ በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር ወረደ በአካለ ነፍስ ደግሞ ወደ ሲኦል ወረዶ በሲኦል ለነበሩ ነፍሳት ነፃነትን አወጀላቸው፡፡ መለኮት፥ በተዋሕዶ፥ ከሥጋም ከነፍስም ጋር ነበረ፡፡ በታላቅ ኃይልና ሥልጣንም ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ “ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ” በቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ላይ እንዲሁም ምዕመናንና ምዕመናት ሰላምታ ከመለዋወጥ አስቀድሞ ይህን ቃል በመናገር የትንሣኤውን አዋጅ ማወጅና መመስከር ይገባቸዋል፡፡
“እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፥ የወይን ስካር እንደ ተወው እንደ ኃያልም ሰው፤ ጠላቶቹንም በኋላቸው መታ፤ የዘላለምን ኀሣር ሰጣቸው።” መዝ 78: 65-66
ዕለተ ቀዳሚት ሥዑር
በዚህች ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሰ መቃብር ዐርፎ የዋለባት ዕለት በመሆኗ ‹‹ቀዳሚት ሥዑር›› ትሰኛለች፡፡ ‹‹ቀዳሚት ሥዑር›› የተባለችበት ምክንያትም በዓመት አንድ ቀን ስለ ምትጾም ነው፡፡
የዘንድሮን የትንሳዔ በዓል ምክንያት በማድረግ በዋዜማው ቅዳሜ ሚያዚያ 26 ቀን 2016 ዓ/ም (04. mai 2024) ከምሽቱ 20:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 0300 ሰዓት ድረስ የማህሌት፣ የዝማሬና የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ይካሄዳል፡፡ ለትራንስፖርት እንዲያመች ቤ/ክርስቲያኑ እስክ ጠዋቱ 06:00 ሰዓት ድረስ ከፍት ሆኖ ይሆናል።
የሰሙነ ሕማማት አምስተኛው ቀን ዕለተ ዓርብ”ስቅለት”
ዕለተ ዓርብ እኛ የሰው ልጆች በኃጢአት ቁራኝነት እንኖርበት የነበረው የጨለማ ሕይወት ያከተመባትና ፍጹም ድኅነት ያገኘንባት ታላቅ ዕለት ናት፡፡ ዕለቱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ሁሉ መድኃኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልእልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበት ታላቅ ቀን ነው፡፡ ማቴ.27-35-75፡፡
ጸሎተ ሐሙስ/ ህጥበተ እግር
ጸሎተ ሐሙስ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ መኾኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ቀን በመሆኑ “ጸሎተ ሐሙስ” ይባላል (ማቴ. ፳፮፥፴፮–፶፮)፡፡ ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ምሥጢረ ቍርባንም በዚህ ቀን ተመሥርቷልና ዕለቱ “የምሥጢር ቀን” ይባላል ሉቃስ 22፥14-20፡፡ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ዮሐንስ ወንጌል -13:4-17 ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ዅሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ የንጽሕና፣ የቅድስና አምላክ መኾኑን ያሳያል፡፡
ሰሞነ ህማማት
ከሆሳዕና ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡ የዘንድሮው ሰሞነ ህማማት ክሰኞ ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ/ም (29. april 2024) ይጀምራል።
ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል የተቀበለውን መከራና ፍዳ በማስታወስ ክርስቲያኖች የክርስቶስን ውለታ እያሰቡ እጅግ የሚያዝኑበት፣ የሚያለቅሱበት፣ የሚሰግዱበት፣ ከሌላው ቀናትና ጊዚያት በተለየ መልኩ አምላካቸውን የሚማፀኑበት፣ ጥዋት ማታ አምላካቸውን ደጅ የሚጠኑበት፣ ሀጢያታቸውን በቤተክርስቲያን አደባባይ ለካህኑ የሚናዘዙበት ሳምንት ነው፡፡
በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። ትንቢተ ኢሳይያስ – ምዕራፍ 53:5
“ሆሳዕና” የዐብይ ጾም ስምንተኛው ሳምንት
የጌታችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሣኤ በዓል ከማክበራችን በፊት ያለው ሰንበት ሆሳዕና ተብሎ ይጠራል፤ በዚህ ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጫ ተቀምጦ በታላቅ ክብር ወደ ኢየሩሳሌም የገባበት ቀን ይዘከራል፡፡ «አንች የጽዮን ልጅ አትፍሪ፤ እነሆ ንጉሥሽ በእህያ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ይመጣል» ተብሎ እንደተጻፈ ኢየሱስ የአህያ ውርንጫ አግኝቶ በእርሱ ተቀመጠ ዮሐ.12፥ 14-15፡፡
በዚያ ዘመን የነበሩት ሰዎች በሆሳዕና ቀን ዘምረውና ክርስቶስን አሞግሰው፣ በስቅለተ ዓርብ ቀን (ከአምስት ቀናት በኋላ) ግን «ይሰቀል» ብለው አብዝተው ጮሁ፡፡ በሆሳዕና ቀን «ንጉሣችን» ብለው ዘምረው በስቅለተ-ዓርብ ቀን ደግሞ «ደመኛችን ነው» አሉ፤ ……..
ኒቆዲሞስ – የዐብይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት
በቤተክርስቲያናችን የበዓላት ቀኖና መሰረት ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሰንበት ኒቆዲሞስ ይባላል፡፡ኒቆዲሞስ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ድል ማድረግን ወይም አሸናፊነትን ያመለክታል። ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፥ ከአይሁድ አለቆችና መምህራና አንዱ ሲሆን በለሊት ወደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ እየሄደ ሰለ ሚስጥረ ጥምቀት፣ ሚስጥረ ሥላሴ፣ ሚስጥረ ሥጋዌና ሚስጥረ ትንሳኤ ሙታን መማሩን የሚነገርበት በተለይ ሳምንቱ ስለኒቆዲሞስ ስብእና የሚነበብበት፣ የሚተረጎምበትና የሚሰበክበት ሳምንት ነው። (ዮሐ 3 : 1- 12)
“ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም። የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው” መዝ 17:3-4
“ገብር ሔር” የዐቢይ ጾም ስድስተኛው ሳምንት
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስያሜ መሠረት የዐቢይ ጾም ስድስተኛው እሑድ ወይም ሳምንት ገብር ሔር ይባላል፡፡ ገብር ሔር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ መስሎ ካስተማራቸው ትምህርቶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ ታልቅ ትምህርት በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 25፥14-25 ላይ ይገኛል።
“አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው። በታላቅ ጉባኤ ጽድቅን አወራሁ፤” መዝሙረ ዳዊት – ምዕራፍ 39:8