ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች

ጾመ_ነቢያት!

እግዚአብሔር አምላካችን ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ መልበሱን፣ ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ወደ ግብጽ ግብር መሰደዱን፣ በባሕረ ዮርዳኖስ መጠመቁን፣ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ማብራቱን፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል ልዩ ልዩ ዓይነት መከራ መቀበሉን፣ መሰቀሉን፣ መሞቱን፣ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ ማረጉንና ዳግም ለፍርድ የሚመጣ መኾኑን በአጠቃላይ የማዳን ሥራውን በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው አስቀደመው በትንቢት ተናግረዋል፡፡

የአምስት ዓመት መሪ እቅድ (2025 – 2030)

የማሀደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ ከ 2025 – 2030 የአምስት ዓመት መሪ ዕቅድ የተዘጋጀውን ረቂቅ ማብራሪያ በመስጠት ከቤተ ክርስቲያኒቱ ምዕመናን እና ምዕመናት ጋር በዛሬ ዕለት ዕሑድ ጥቅምት 10 ቀን ከሰንበት ቀዳሴ ሥነ ስርዓት በኋላ ዉይይት ተደርጓል፡፡ በዚሁም መሰረት የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው መልስ የተሰጠባቸው ሲሆን ለመሪ ዕቅዱ እንደግብአት የሚጠቅሙ ሃሳቦችም ተሰንዝረዋል።

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!

“የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።” 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡18
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤ/ክ በየዓመቱ መስከረም 16 ቀን (26. september) የመስቀል በዓል በዋዜማው የደመራን ችቦ በማብራት በደመቀ ሁኔታ ይከበራል፡፡ በዓሉ የንጉስ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ፣ ደመራ አስደምራ በእሳት ባቀጣጠለችው ጊዜ፣ ጢሱ ወደ ላይ ከወጣ በኋላ ተመልሶ ያረፈበትን ሥፍራ አስቆፍራ ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ማግኘቷን በማስመልከት በየዓመቱ የሚከበር ታላቅ ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓል ነው፡፡

እንኳን ከዘመነ ዮሃንስ ወደ ዘመነ ማቴዮስ በሰላም እና በጤና አሸጋገራችሁ!

“በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል” መዝ – ምዕራፍ 65:11
አዲሱ ዘመን የሰላም የጤና የንስሀ እንዲሆንላችሁ እየተመኘን አዲሱን ዘመን በማስመልከት በዕለቱ ረቡዕ መስከረም 1 ቀን ከቀኑ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በቅዳሴ እና በዝማሬ እንዲሁም በትምህርተ ወንጌል በደብራችን በማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ይከበራል።
በኦስሎና አካባቢዋ የምትገኙ ምዕመናንና መዕመናት በቦታው በመገኘት የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የደብሩ ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጽህፈት ቤት በማክበር ይጋብዛል።

የስዊድን፤ ስካንዲናቪያን እና ግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት የ2016 ዓ/ም ጠቅላላ ጉባኤ

በስዊድን፤ ስካንዲናቪያን እና ግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ጷጉሜ 1 እና 2 ቀን 2016 ዓ/ም በስቶክሆልም መንበረ ጵጵስና ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ሲያካሄድ የቆየውን ጠቅላላ ጉባኤ አጠንቆ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

ጷጉሜ(ጷጉሜን) እንኳን ለትንሿ የበረከት ውርሃ ጳግሜ በሰላም አደረሳችሁ!

በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጷጉሜን የወር ተጨማሪ ሳይሆን የዓመት ተጨማሪ በማድረግ ወሮቹን 30 ቀን፣ የዓመቱንም ቀን ቁጥር ደግሞ ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ቀን አድርገው ሰይመውታል፡፡ ጷጉሜን የሚለው ስያሜዋ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን “ኤፓጉሜኔ” ማለት ጭማሪ ማለት ነው ፡፡ በግእዝ ቋንቋችን ተውሳክ ማለት ነው፡፡ ተውሳክ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው፡፡
በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጷጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡

እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የደብረ ታቦር (የቡሄ) በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤ/ክ ቀኖና መሰረት ከዘጠኙ አብይ በዓላት ውስጥ አንዱ ሲሆን የሚከበረውም ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በማስተማር በነበረበት ጊዜ በደብረ ታቦር ላይ ብርሃነ መለኮቱን ክብረ መንግስቱን የገለፀበት ዕለትን ለማስታወስ ነው። ይህ በዐል በየአመቱ ነሃሴ ፲፫ (13) ቀን ይከበራል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጾመ ፍልሰታን በማስመልከት መልእክት፣ ቃለ በረከትና ቡራኬ አስተላለፉ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! በሀገር ውስጥና በተለያዩ ክፍለ ዓለማት የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ! በማሕፀነ ማርያም በፈጸመው እውነተኛ ተዋሕዶ የሰው ልጅን ከኃሣር ወደ ክብር የመለሰ እግዚአብሔር አምላካችን፣ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ስድስት ዓመተ ምሕረት ጾመ ቅድስት ማርያም በደኅና አደረሰን አደረሳችሁ!፤ ‹‹ተፈሥሒ ኦ ምልእተ ጸጋ፣ ተፈሥሒ እስመ […]

እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በስለም አደረሳችሁ፣ አደረሰን አሜን!

ጾመ ፍልሰታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 64 ዓመት በዚች ምድር ኖራ እንደ አንድ ልጇ መሞቷን፣ መነሳቷንና ማረጓን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት የጾሙት ጾም ነው። ጾሙን ነሐሴ 1 ቀን ጀምረው በነሐሴ አሥራ አራት ቀን ጌታችን እመቤታችንን አምጠቶ እንድትገለጥላቸው አደረገ፤ ቀበሯትም፡፡ በነሐሴ አሥራ ስድስት ቀንም እርገቷን አከበሩ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በቤተክርስቲያናችን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ከነሐሴ 1 ቀን እስከ ነሐሴ 16 ቀን ጾመ ፍልሰታ በመባል ይጾማል፡፡
በቤተ ክርስቲያን ተግኝታችሁ ጸሎት ለማድረግ የምትፈልጉ መዕመናንና መዕመናት ከዛሬ ረቡዕ ነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 7:00 ሰዓት ጀምሮ ቤ/ክ ክፍት መሆኑን እየገለጽን የየዕለቱን የውዳሴ ማርያም ትርጉም በንባብ የሚቀርብ መሆኑን እንሳታውቃለን።

እንኳን ለሊቀ መላኩ ቅዱስ ዑራኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን !

ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ጥበብን አጠጥቶ ሰማያዊውን ምሥጢር የገለጠለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ በመሆኑም ሐምሌ 22 ቀን ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበትና ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል የዕውቀትን ጽዋ ያጠጣበትን ዕለት የሚከበርበትና የሚዘከርበት ዕለት ነው። ጥር 22 በዓለ ሲመቱ ነው። መጋቢት 27 የጌታችንን ክቡር የሆነ ወርቀ ደሙን ለዓለም የረጨበት ዕለት ነው።
ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ዑርኤል በመብረቅ በነጐድጓድ የተሾመ ነው። መጽሐፈ ሄኖክ 6:2

በፌስቡክ ያግኙን

አባልነት

በአባልነት ለመመዝገብ የምትፈልጉ የአባልነት ፎርምና ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት

የገንዘብ አስተዋጻኦ

የባንክ ሂሳብ ቁጥር፡ 1503 622 909

111030

በቋሚነት

በቋሚነት በየወሩ በቀጥታ በባንክ አካውንት ወይንም በቪፕስ ለመክፈል

Minside

ስለ እኛ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ የማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ በጥቂት ግለሰቦች አነሳሽነትና በእግዚአብሔር ፈቃድ መጋቢት 6 ቀን 2007 ዓ/ም ተመሠረተ፡፡ በወቅቱ የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ እንጦስ በቦታው ተገኝተው ቤተ ክርስቲያኑን ባርከውና ቀድሰው መሠረት ከመጣላቸውም በላይ በቀጣይነት ከአንድ ዓመት በኋላ የሊቀ መላኩን የቅዱስ ገብርኤል ጽላት በማስመጣት ለቤ/ክርስቲያኑ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ሲመሰረት 19 ምዕመናንና ምዕመናት በአባልነት ተመዝግበው የነበሩት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የአባላት ቁጥር ከ200 በላይ ሆኗል፡፡ ቋሚ ቤ/ክ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ለጊዜው በኪራይ ቀደም ሲል በካምፐን ሜኒሄትስ ሁስና በካምፐን ሺርከ አሁን ደግሞ በCaspar Storms vei 12, 0664 Oslo, የሰንበት ቅዳሴ፣ የሰንበት ት/ቤትና እንዲሁም የበዓላት መርሃ ግብር ሳይታጎሉ ቤተ ክርስቲያኑ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ ያልተቋረጠ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

ፎቶ፦ ብጹዕ አቡነ እንጦስ ቤተክርስቲያናችህንን ባርከው አገልግሎት ሲያስጀምሩ

ያግኙን

  • Tel: +47 462 21 386
  • Epost: post@lidetalemariam.no
  • Postadresse: Jerikoveiene 93A, 1052 Oslo
  • Besøkadresse: Caspar Storms vei 12, 0664 Oslo
  • Org.nr. 915 237 118
  • Bank Account: 1503 622 9095
  • Vipps: 111030