የሀዘን መግለጫና የጸሎት መርሐ-ግብር ጥሪ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
“መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫውን ጨርሻለሁ፤ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ።” (2ኛ ጢሞ. 4፥7)
እጅግ የምንወደውና የምናከብረው ወንድማችን ኢንጂነር መስፍን ኃይሌ፣ በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዚህች ዕለት
ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል። ወንድማችን ኢንጂነር መስፍን ኃይሌ ባለ ትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ አባት
የነበረ ሲሆን፤ በማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን
ምሥረታ ጀምሮ ቤተክርስቲያንን በፍጹም ቅንነት፣ በትጋትና በታማኝነት ሲያገለግል የቆየ
ተወዳጅ ወንድማችን ነበር። ቤተክርስቲያናችን በወንድማችን ማረፍ የተሰማትን ጥልቅና መራራ ሀዘን
እየገለጸች፤ ለባለቤቱ፣ ለልጁ እንዲሁም ለመላው ቤተሰቦቹና ወዳጅ ዘመዶቹ እግዚአብሔር አምላክ
መጽናናትን እንዲሰጥ ትጸልያለች።
በመሆኑም የወንድማችንን ሕይወት የምናስብበትና ለቤተሰቦቹ የሀዘን ማጽናኛ የምንሰጥበት
መርሐ-ግብር በቤተክርስቲያናችን ደጀ-ሰላም ተዘጋጅቷል።
ወዳጅ ዘመዶቻችሁ ሁሉ በቦታው በመገኘት በጸሎትና በሐዘን እንድታጽናኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
የማጽናኛ መርሐ-ግብር ሰዓታት፦
ቀን – የሰዓት ገደብ
ሐሙስ 05 Feb – ከ 18:00 – 21:00
ዓርብ 06 Feb – ከ 14:00 – 21:00
ቅዳሜ 07 Feb – ከ 14:00 – 21:00
እሁድ 08 Feb – ከ 14:00 – 21:00
አድራሻ – Caspar Storms vei 12, Oslo
የወንድማችንን ነፍስ በአብርሃም በይስሐቅና በያዕቆብ እቅፍ ያኑርልን።
ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን
