
ኒቆዲሞስ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ድል ማድረግን ወይም አሸናፊነትን ያመለክታል፡:
ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፥ ከአይሁድ አለቆችና መምህራን አንዱ ነው። በወንጌለ ዮሐንስ ምዕራፍ ሦስት ከፈሪሳውያንወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ የተባለ አንድ ሰውእንደነበረና እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን መጥቶ እንደተማረተጠቅሷል። (ዮሐ ፩–፪)በአይሁድ አለቆች ፊትም ”ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማየሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” በማለት ስለ ክርስቶስ የተናገረ እሱ ነው። እነርሱ ግን በክርስቶስ ያመኑበት ኦሪትን የማያዉቁ ስሑታን እንደሆኑ ያስቡ ስለ ነበር ”አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ከገሊላ ነቢይ እንደማይነሳ መርምርና እይ“ አሉት እንጂ አልተቀበሉትም። ዮሐ፯፥፵፰–፶፪።
ኒቆዲሞስ የአርማትያስ ሰው ከሚሆን ከዮሴፍ ጋርበመሆን የጌታችንን ቅዱስ ሥጋ በንጹሕ በፍታ ገንዞ በአዲስመቃብር ቀብሯል። ወንጌላዊው ዮሐንስ ”ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ሄዶ የነበረዉ ኒቆዲሞስም መጣ፤ ቀብተውም የሚቀበርበትን መቶ ወቄት የከርቤና የሬት ቅልቅል ሽቶ አመጣ።” እንዳለ። ዮሐ ፲፱፥፴፱። በዚህም ኒቆዲሞስ ከምክረ አይሁድ ያልተቀላቀለ መሆኑ ይታወቃል። የሌሊት ተማሪው ኒቆዲሞስ የሌሊቱን ጊዜ ለትምህርት ለምንመረጠ የሌሊት ተማሪው ኒቆዲሞስ ዮሃ ፫፤፪ከፈሪሳዊያን ወገን የሆነ የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባልአንድ ሰው በሌሊት ወደ ጌታ እየሄደ ይማር ነበር ኒቆዲሞስ ከቀኑክፍለ ጊዜ ይልቅ የሌሊቱን ጊዜ ለትምህርት ለምን መረጠ ?
፩/ ኒቆዲሞስ መምህር ስለነበር ስማር ሰዎች ቢያዩኝ ውዳሴከንቱ መምህር መባል ይቀርብኛል ብሎ ነው እኛስ ዛሬ የዘላለምህይወት የሚሰጠንን ቅዱስ ቃል ብትህትና መማር ሲገባንለምድራዊ ክብር ብለን በቀን ጊዜያችን መማር ያልቻልን ስንቶቻችን ነን ስለዚህ ቀን ጊዜአችንን በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል።‹ ማንም ሊሰራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለችና › ዮሃ ፱፤፬፪/ .ኒቆዲሞስ የአይሁድ መምህር ስለነበር እንዳያዩት ፈርቶ ሌሊት እየመጣ ይማር ነበር እኛስ ዛሬ ልባችን የተረዳውን እውነት በግልጥ እንዳንፈጽም በፍራቻ በይሉኝታ የምንሰውር ስንቶቻችን ነን‹ፍጹም ፍቅር ፍርሃት የለውም ፍርሃት ቅጣት አለውና› ፩ዮሃ፬፤፲፰ ፍርሃትን አስወግደን ለእውነት ልንቆም ይገባል።
፫/ ኒቆዲሞስ ከቀን ልብ ይልቅ የሌሊት ልብ የተካተተ ስለሆነ በሙሉ ልቡ በማስተዋል ለመማር ስለፈለገ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የማታውን መረጠ ዛሬስ ስንቶቻችን ነን ቅዱስ ቃሉን በማስተዋል ከልብ ሆነን የምንማር የሰማነው ቅዱስ ቃል በህይወታችን ፍሬ እንዲያፈራ ቅዱስ ቃሉን ከልብ ሆነን በማስተዋል ልንሰማ ይገባናል ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ልብ መልካም መሬት ተብⶀል‹ በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውልነው› ማቴ ፲፫፡፳፫ አንዳንዶቻችን እያደረግን እንኳን አንደበታችን የእግዚአብሄርን ቃል ይነዳል ልባችን ሌላ ቦታ ይንጎዳጎዳል በማህበር ጸሎትም አብረን እየጸልይን በመሃል ሳይን አውት አርገንልክ ሲፈጸም አለቀ እንዴ ብለን ሳይን ኢን የምናደርግ አንጠፋም።�
፬/ ሌሊት ጨለማ ነው ብርሃን የለም ይህም የኃጢአት ምሳሌነው ኒቆዲሞስ በሌሊት መምጣቱ በኃጢአት እንዳለ ንስሃ እንደሚፈግ ያስረዳናል ዛሬስ ስንቶቻችን ነን ቅዱስ ቃሉን ስንሰማ በተአምኖ ኃጢአት በንስሃ ውስጥ ሆነን የምንሰማ ያለንስሃ የምንሰማው ቃል በህይወታችን ፍሬ የማፍራት እድሉ ጠባብ ነው ምክንያቱም በንስሃ ከልባችን ያልጸዱት ክፉምኞቶች እንደ እሾህ ሆነው ያንቁታልና‹ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ እሾህም ወጣና አነቀው› ማቴ፲፫፤፰ ተብሎ የተጻፈው ለዚህ ነው።�
፭/ ሌሊት የቆየው ኪዳን ወይም የብሉይ ኪዳን ምሳሌ ነው ኒቆዲሞስም እኔ ምሁረ ኦሪት እንጂ ምሁረ ወንጌል አይደለሁም ወንጌልን ካንተ እማር ዘንድ ያስፈልገኛል ሲል በሌሊት ይመጣነበር ብሉያት ከሓዲሳት ጋር ተዋህደው ሲተረጎሙ ሰሙና ወርቁ ተጣምሮ የሕይወት ትምህርት ያስገኛል አንዳንዶች ዛሬ ብሉያት ጭራሽ አያስፈልጉም ሲሉ ይደመጣሉ ነገር ግን እንደ ኒቆዲሞስ ሁለቱን ኪዳናት አዋህዶ መጓዝ ትክክለኛው መንገድ ነውለዚህም ነው ጌታ ሲያስተምር ‹እውነት እላችኋለው ሰማይና ምድረ ስኪያልፍ ድረስ ከህግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ አታልፍም› ማቴ፭፤፲፰ በማለት አበክሮ የተናገረውኒቆዲሞስ ምንም እንኳን የቀኑ ክፍለ ጊዜ ባይመቸውም በሌሊቱሰአት ለመማር ችⶀል እኛም ከሱ ተምረን ከልብ ካለቀሱ እንባአይጠፋምና ምንም ስራ ቢበዛብን ለቅዱስ ቃሉ ጊዜአይጠፋምና ህይወት ለሚገኝበት ትምህርት ጊዜ ልንሰት ይገባል።