እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ቤዛ ኩሉ አለም ዮም ተወልደ / የዓለም ሁሉ ቤዛ ዛሬ ተወለደ!

እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። የሉቃስ ወንጌል – ምዕራፍ 2:10-11

የዘንድሮን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ ሰኞ ታህሳስ 28 ቀን 2024 ዓ/ም ከምሽቱ 20:00 ሰዓት ጀምሮ በማህሌት፣ በዝማሬ፣ በቅዳሴና ሌሎች የተለያዩ መርሃ ግብሮች በቤተ ክርስቲያናችን ተከብሮ ይውላል።

በኦስሎና አካባቢው የምትገኙ ምዕመናንና ምዕመናት በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ተገኝታችሁ በዓሉን በጋራ እንድናከብር የደብሩ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ በማክበር ይጋብዛል!