እንኳን ከዘመነ ዮሃንስ ወደ ዘመነ ማቴዮስ በሰላም እና በጤና አሸጋገራችሁ!
“በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል” መዝ – ምዕራፍ 65:11
አዲሱ ዘመን የሰላም የጤና የንስሀ እንዲሆንላችሁ እየተመኘን አዲሱን ዘመን በማስመልከት በዕለቱ ረቡዕ መስከረም 1 ቀን ከቀኑ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በቅዳሴ እና በዝማሬ እንዲሁም በትምህርተ ወንጌል በደብራችን በማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ይከበራል።
በኦስሎና አካባቢዋ የምትገኙ ምዕመናንና መዕመናት በቦታው በመገኘት የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የደብሩ ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጽህፈት ቤት በማክበር ይጋብዛል።
አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የፍትህ ዘመን እንዲሆንልን፣ ሃገራችንንና ቤተ ከርስቲያናችንን እንዲጠብቅልን የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ጥበቃና ተራዳኢነት፣ የቅዱሳን አባቶች ጸጋና በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን!